የህዝብ አስተያየት ዳሰሳ

CCFP RFP I - የፈንድ ዓይነት: የፋይናንስ መረጋጋት

 

የውጤት መግለጫ: ከግል ወይም ከመንግስት ድርጅቶች በሚሰጥ አነስተኛ ወይም ያለምንም የፋይናንስ ድጋፍ ወይም ድጎማዎች በቋሚነት መሰረታዊ ፍላጎታቸውን ማሟላት የሚችሉበት በቂ ገቢ የማግኘት እና የማስቀጠል ችሎታ እንዲኖር።

 

የአገልግሎት ምሳሌዎች (ከሚከተሉት ምሳሌዎች የተወሰኑትን ሊያካትት ይችላል፣ ነገር ግን በነዚህ ብቻ የተወሰነ አይደለም)

  • ሊከሰት የሚችልን የፋይናንስ ቀውስ አስቀድሞ ለማየት እና ለመከላከል የፋይናንስ ሊትሬሲ/አስተዳደር ስልጠና እና የምክር አገልግሎት
  • የፋይናንስ ምክር አገልግሎት
  • የፋይናንስ ሀብት ፈጠራ
  • ወደ ስራ ኃይል እየተሸጋገሩ ላሉ የቤተሠብ አባላት ወጪው ተመጣጣኝ የሆነ፣ ተደራሸሰነት እና ጥራት ያለው የህጻን ክብካቤ
  • የህግ አገልግሎቶች
  • የስራ በቅጥር ድጋፍ፣ የስራው እና የስራ ፈጠራ ስልጠና
  • የፋይናንስ ብዝበዛን የመከላከል አገልግሎቶች
 

እባክዎ ስለታቀደው የፋይናንስ ማረጋጊያ አይነት የእርስዎን አስተያየቶች ያጋሩ።

Closed for Comments

CCFP RFP I - የፈንድ አይነት: ምግብ እና ስነምግብ

 

የውጤት መግለጫ: ለበቂ፣ በዋጋው ተመጣጣኝ እና መጋቢነት ላለው ምግብ አስተማማኝነት እና ቀጣይነት ባለው መልኩ ተደራሽ መሆን። ስለ ጤናማ እና መጋቢነት ስላለው ምግብ የመረጃ እና የትምህርት ተደራሽነት ማግኘት እና ጤናማ አመጋገብን ለማጎልበት እውቀትን እና መረጃን የማጎልበት እድል ማግኘት።

 

 

 

የአገልግሎት ምሳሌዎች (ከሚከተሉት ምሳሌዎች የተወሰኑትን ሊያካትት ይችላል፣ ነገር ግን በነዚህ ብቻ የተወሰነ አይደለም)

 

  • የስነምግብ ትምህርት ፕሮግራሞች
  • የአርሶ አደሮች ገበያ፣ የምግብ ህብረት ስራ ማህበራት፣ ተንቀሳቃሽ ገበያዎች፣ የቀጠና ማከፋፈያ ቦታዎች፣ የማህበረሰብ የአትክት ስፍራዎች
  • ስለ ራስ መቻል የጉዳይ አስተዳደር አገልግሎቶችን የሚሰጡ የምግብ አቅርቦት ፕሮግራሞች

እባክዎ ስለታቀደው የምግብ እና የስነምግብ አይነት የእርስዎን አስተያየቶች ያጋሩ።

Closed for Comments

CCFP RFP I - የፈንድ አይነት: ጤና

 

የውጤት መግለጫ: የተቀዳሚ፣ ልዩ፣ ቃላዊ፣ ባህሪያዊ እና የረጅም ጊዜ የጤና ክብካቤ፣ በተለይም የበሽታ መከላከል አግልግሎቶች ተደራሽ መሆን። ጤናማ ባህሪያትን ተግባራዊ ለማድረግ እና በሽታን እና ጎጂ የጤና ሁኔታዎችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚያስችል እርምጃ ለመውሰድ አስፈላጊውን እውቀት እና መረጃዎችን ለማጎልበት።

 

የአገልግሎት ምሳሌዎች (ከሚከተሉት ምሳሌዎች የተወሰኑትን ሊያካትት ይችላል፣ ነገር ግን በነዚህ ብቻ የተወሰነ አይደለም)

 

  • የጤና ክብካቤ የዋጋ ተመጣጣኝት እና የአገልግሎቶች ተደራሽነት፣ በተለይም ቃላዊ የእይታ እና የድምጽ
  • የጤና አውደ ርዕይ እና የጤና ምርመራ ክሊኒኮች፣ የጥርስ ህክምና ክሊኒኮች፣ ክትባቶች፣ የስነ ምግብ ትምህርት
  • ተቀዳሚ የጤና/የጥርስ ህክምና አገልግሎቶች እና ልዩ ክብካቤ
  • የባህሪ ጤና አገልግሎቶች (ለምሳሌ ራስን ማጥፋትን መከላከል፣ የአዕምሮ ጤና፣ አደንዛዥ እጥ መከላከል.ማገገም)
  • እድሜያቸው ከፍ ያ ሰዎች/የአረጋዊያን የጤና ክብካቤ (ለምሳሌ የረጅም ጊዜ ማስታመሚያ ማዕከል፣ የቤት ውስጥ ክብካቤ)
  • አነስተኛ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ችሎታ ላላቸው እና ሁሉም የችሎታ ደረጃ ላላቸው ሰዎች የጤና አገልግሎቶችን ተደራሽነት የሚያሳድጉ ፕሮግራሞች እና አገልግሎቶች

እባክዎ ስለታቀደው የጤና አይነት የእርስዎን አስተያየቶች ያጋሩ።

 

Closed for Comments

CCFP RFP I - የፈንድ አይነት: Hቤት

 

የውጤት መግለጫ: ከሌሎች መሰረታዊ ፍላጎቶች ጎን ለጎን ደህንነቱ የተጠበቀ፣ የተረጋጋ እና ተደራሽ የሆነ መኖርያ ማግኘት። በማህበረሰቡ ውስጥ በተቻለ መጠን ራስን ችሎ ለመኖር አስፈላጊ ከሆኑ የድጋፍ አገልግሎቶች ጋር ዋጋው ተመጣጣኝ የሆነ ተደራሽ የሆነ መኖርያ ቤት ማግኘት።

 

የአገልግሎት ምሳሌዎች (ከሚከተሉት ምሳሌዎች የተወሰኑትን ሊያካትት ይችላል፣ ነገር ግን በነዚህ ብቻ የተወሰነ አይደለም)

 

  • የተረጋጋ የመኖርያ ቤት ለማግኘት እና የተከራዮችን ራስን ችሎ የመኖር ችሎታን ለማሳደግ የሚደረጉ የድጋፍ አገልግሎቶች (ለምሳሌ የጉዳይ አስተዳደር፣ የአእምሮ ጤና፣ አልኮል እና የእጽ ተጠቃሚነት፣ ራስን ችሎ መኖር፣ የቤት ውስጥ የጤና ጉብኝቶች፣ የሙያ፣ የጤና፣ የቤ እቃ እና ሌሎች የቤት እቃዎች፣ የአቻ ድጋፍ እና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች)
  • ከተቋማዊ ክብካቤ ወደ ቤት ውስጥ ወይም ማህበረሰብ ተኮር ክብካቤ የሚሸጋገሩ ግለሰቦችን የመርዳት አገልግሎቶች
  • አረጋዊያን እና ልዩ ፍላጎቶች ያላቸው ሰዎች ያሏቸውን እድሎች ጨምሮ ግለሰቦች እና ቤተሰቦች በቂ የድጋፍ ኔትወርኮች እና አገልግሎቶች ያለው መኖርያ ቤት በማህበረሰባቱ ውስጥ እንዲያገኙ የመርዳት አገልግሎቶች
  • አነስተኛ ገቢ ላቸው አረጋዊያን፣ ሁሉንም አይነት የችሎታ ደረጃ ያላቸው ሰዎች ወይም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች ወጪ ተመጣጣኝ የሆነ መኖርያ ቤትን ለማስጠበቅ የሚያስፈልግን ተደራሽ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ ወይም መሰረታዊ ጉዳዮችን ያሟላ መኖርያ ቤት ለማሟላት አባወራዎች የአነስተኛ ገቢ መኖርያ ቤት መልሶ ግንባታ፣ ጥገና እና ምትክ ቤቶችን እንዲያገኙ የመርዳት አገልግሎቶች

 

እባክዎ ስለታቀደው የቤት አይነት የእርስዎን አስተያየቶች ያጋሩ።

 

Closed for Comments

CCFP RFP I - የፈንድ አይነት: የተማረ የሰው ኃይል/የትምህርት ልማት/ስኬት

 

የውጤት መግለጫ: በትምህርት እና ሙያ ስኬት ፋይናንስን የማስተዳደር እና የስራ ግቦችን ለማሳካት ውጤታማ የሆነ የማንበብ፣ የመጻፍ እና የመግባባት ችሎታ እንዲኖረው። ሥራን/የስራ ቅጥርን እና ራስን ችሎ የመኖር ክህሎቶችን ለማጎልበት ጥራት ያለው የህጻን ክብካቤ እና ትምህርት እና ድጋፍ ተደራሽ ለመሆን።

 

የአገልግሎት ምሳሌዎች (ከሚከተሉት ምሳሌዎች የተወሰኑትን ሊያካትት ይችላል፣ ነገር ግን በነዚህ ብቻ የተወሰነ አይደለም)

 

  • የእንሊዘኛ ቋንቋ ብቃት አገልግሎቶች እና/ወይም ትምህርት
  • የቅድመ ህጻንነት እድገት አገልግሎቶች
  • ራስን ችሎ ለመኖር የሚያስፈልጉ ችሎታዎች ሁሉ ያላቸውን ግለሰቦች ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመርዳት የስራ እና የስልጠና ክህሎቶችን የሚሰጡ አገልግሎቶች
  • የጎልማሶች ትምህርት፣ እውቅና
  • ደጋፊ የስራ ቅጥር
  • ዱጂታዊ ተደራሽነት እና የትምህር ፕሮግራሞች
  • አካል ጉዳተኝነት ያለባቸው ግለሰቦች ይህን ውጤት ለማሟላት ያሏቸውን አይነተኛ ፍላጎቶች የሚያካትቱ አገልግሎቶች

እባክዎ ስለታቀደው የተማረ የሰው ሀይል/የትምህርት ልማት/ስኬት አይነት የእርስዎን አስተያየት ያጋሩ።

 

Closed for Comments

CCFP RFP I - የፈንድ አይነት: አወንታዊ ባህሪዎች እና ጤናማ ግንኙነቶች

 

የውጤት መግለጫ: ከጥቃት፣ ቸል ከመባል እና ከስቃይ ነጻ የሆኑ እና ደኅንነታቸው የተጠበቀ አወንታዊ ባህሪዎችን እና ጤናማ ግንኙነቶችን ለማጎልበት እና አካላዊ፣ ስሜታዊ፣ አእምሯዊ እና ማህበራዊ ደህንነትን ማሳደግ።

 

የአገልግሎት ምሳሌዎች (ከሚከተሉት ምሳሌዎች የተወሰኑትን ሊያካትት ይችላል፣ ነገር ግን በነዚህ ብቻ የተወሰነ አይደለም)

 

  • የማማከር አገልግሎቶች
  • የግጭት አፈታት እና ንዴትን የመቆጣጠር ስልጠና እና የማማከር አገልግሎት
  • በአወንታዊ ባህሪያት እና ጤናማ ግንኙነቶች ላይ ያተኮሩ ወጣት ተኮር የመከላከል ፕሮግራሞች እና አገልግሎቶች
  • ከስቃይ የማገገም አገልግሎቶች
  • የቤት ውስጥ ድብደባ እና የወሲባዊ ጥቃት መከላከያ እና ማገገምያ አገልግሎቶች
  • ውስን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ችሎታ እና ሁሉም አይነት ችሎታ ያላቸውን ግለሰቦች ፍላጎቶች የሚዳስሱ ፕሮግራሞች እና አገልግሎቶች

እባክዎ ስለታቀደው የአወንታዊ ባህሪያት እና ጤናማ ግንኙነቶች አይነት የእርስዎን አስተያየት ያጋሩ።

 

Closed for Comments

CCFP RFP I - የፈንድ አይነት: ድጋፍ/ማህበረሰብ/ማህበራዊ ትስስሮች

 

የውጤት መግለጫ: ማህበረሰብ ተኮር ትራንስፖርት እና የህጻን ክብካቤን ጨምሮ ለአካባቢያዊ አገልግሎቶች ተደራሽ መሆን እና የጋራ እና ማህበራዊ ግንኙነቶችን የመፍጠር እና የማስቀጠል ችሎታ።

 

የአገልግሎት ምሳሌዎች (ከሚከተሉት ምሳሌዎች የተወሰኑትን ሊያካትት ይችላል፣ ነገር ግን በነዚህ ብቻ የተወሰነ አይደለም)

 

  • ቡድኖች አወንታዊ መስተጋብር እንዲኖራቸው ለማገዝ ቋንቋን ወይም ባህልን የሚያስተምሩ ኮርሶች
  • የማሰልጠን ፕሮግራሞች
  • ቋንቋ እና ባህል ዘለል ድጋፍ
  • የተገለሉ/ከቤት ውስጥ የማይወጡ ግለሰቦች ማህበራዊ አካባቢዎች
  • ተንከባካቢዎችን ለማገዝ የሚሰጡ የማሳረፍ አገልግሎቶች
  • ወላጆች/አሳዳጊዎች ስራቸውን እየሰሩ እንዲቀጥሉ ለመርዳት የሚያስችል ዋጋው ተመጣጣኝ የሆነ፣ ተደራሽ እና ጥራት ያለው የህጻን ክብካቤ
  • ዋጋው ተመጣጣኝ የሆነ ትራንስፖርት፣ በተለይም ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች
  • አካል ጉዳተኛ ለሆኑ ሰዎች የድጋፍ ፕሮግራሞች
  • የመዝናኛ እንቅስቃሴዎች ተደራሽነት (ለምሳሌ የመዝናኛ ማዕከላት፣ ክፍሎች)
  • የWi-Fi/ኢንተርኔት ተደራሽነት እና የኮምፒዩተር ድጋፍ

እባክዎ ስለታቀደው የድጋፍ/ማህበረሰብ/ማህበራዊ ትስስሮች አይነት የእርስዎን አስተያየት ያጋሩ።

 

Closed for Comments

CCFP RFP II - የፈንድ አይነት: አስቸኴይ የምግብ ድጋፍ

 

የውጤት መግለጫ: በባህሪያቸው የአጭር ጊዜ እና ወሳኝ/አስቸኳይ የሆኑ የምግብ ምደባ እና የተያያዥ ጉዳይ አስተዳደር አገልግሎቶችን የሚሰጡ የምግብ አቅርቦቶች/አገልግሎቶች። አስቸኳይ የምግብ ፕሮግራሞች በጊዜ የተወሰኑ መሆን ያለባቸው ሲሆን ከ6 ወራት በኋላ በድጋሚ የሚገኝ አይደለም። እነዚህ ፕሮግራሞች ቀጥተኛ የተጠቃሚ ድጋፍ ማድረግ አለባቸው።

 

የአገልግሎት ምሳሌዎች (ከሚከተሉት ምሳሌዎች የተወሰኑትን ሊያካትት ይችላል፣ ነገር ግን በነዚህ ብቻ የተወሰነ አይደለም)

 

  • የቀጠና/የተጎራባች ማከፋፈያ ቦታዎች
  • አስቸኳ እና/ወይም የተጨማሪ ምግብ ፕሮግራሞች

 

እባክዎ ስለታቀደው አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ አይነት የእርስዎን አስተያየት ያጋሩ።

Closed for Comments

CCFP RFP II - አስቸኳይ የቤት ድጋፍ

 

የውጤት መግለጫ: የመኖርያ ቤት ችግርን ለመፍታት፣ ከቤት ማስለቀቅን ወይም መፈናቀልን ለመከላከል የሚሰጡ የቤት ድጋፍ አገልግሎቶች። አገልግሎቶች የአጭር ጊዜ ሲሆኑ የረጅም ጊዜ የቤት ፕሮግራም አይደሉም።

 

የአገልግሎት ምሳሌዎች (ከሚከተሉት ምሳሌዎች የተወሰኑትን ሊያካትት ይችላል፣ ነገር ግን በነዚህ ብቻ የተወሰነ አይደለም)

 

  • የአጭር ጊዜ የኪራይ ድጋፍ
  • የፍጆታ ክፍያዎች
  • አነስተኛ ገቢ ላቸው አረጋዊያን፣ ሁሉንም አይነት የችሎታ ደረጃ ያላቸው ሰዎች ወይም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች ወጪ ተመጣጣኝ የሆነ መኖርያ ቤትን ለማስጠበቅ የሚያስፈልግን ተደራሽ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ ወይም መሰረታዊ ጉዳዮችን ያሟላ መኖርያ ቤት ለማሟላት አባወራዎች የአነስተኛ ገቢ መኖርያ ቤት መልሶ ግንባታ፣ ጥገና እና ምትክ ቤቶችን እንዲያገኙ የመርዳት አገልግሎቶች
  • ወጣትን ጨምሮ ጎዳና ተዳዳሪነትን ለቀመሱ ግለሰቦች እና ቤተሰቦች ጊዜያዊ ወይም አስቸኳይ የመጠለያ እና የድጋፍ አገልግሎቶችን መስጠት
  • ከቤት ማስወጣትን ወይም የቤት ቀውስ መከላከልን የሚሸፍኑ ፕሮግራሞች እና የጉዳይ አስተዳደር አገልግሎቶች

 

እባክዎ ስለታቀደው አስቸኳይ የቤት ድጋፍ አይነት የእርስዎን አስተያየት ያጋሩ።

Closed for Comments

የሲሲኤፍፒ የህዝብ አስተያየት ዳሰሳን ስላጠናቀቁ እናመሰግናለን።

ለመውጣት CTRL+W