ማጠቃለያ

Metro በአሁን ሰአት ለ North Link Connections የተንቀሳቃሽነት ፕሮጀክት የተንቀሳቃሽነት ቦርድ አባላት እየመረጠ ነው፡፡ Metro የባስ አገልግሎትን እንዲለውጥ እና አዳዲስ የተንቀሳቃሽነት አማራጮችን እንዲሰራ ለማገዝ እንዲሁም Metro አዲስ ማህበረሰብ ውስጥ መግባት የሚችልበትን መንገድ የሚመክር በአካባው የሚኖር፣ የሚሰራ ወይም የሚጓዝ የማህበረሰብ አባል እየፈለግን ነው፡፡

Metro ከለውጥ ጋር በተያያዠ ውሳኔ በማሳለፍ ውይይቶች ላይ በታክ የተረሱ እና በውሳኔውም የተጎዱ ሰዎችን በፍታዊነት የሚወክል የተንቀሳቃሽነት ቦርድ ለማሰባሰብ አስቧል፡፡

ጥቁር፣ ተወላጅ እና የቀለማት ሰዎች፣ የአካል እና/ወይም የግንዛቤ አካል ጉዳተኛ ሰዎች፣ አነስተኛ ወይም ምንም ገቢ የሌላቸው ሰዎች፣ ጎዳና ተዳዳሪዎች ወይም የቤት ችግር ያለባቸው ሰዎች፣ ጥገኞች እና/ወይም ስደተኞች እና አነስተኛ የእንግሊዝኛ ብቃት ያላቸው ሰዎችን ያካትታል፡፡ Metro ሰዎች እድል የሚያገኙበት እና የሚያጡበት በርካታ ማንነት እንዳላቸው ይረዳል፤ እድል አላገኙም ተብለው የተሰየሙ ቡድኖች North Link Connections የተንቀሳቃሽነት ቦርድ ላይ ለማገልገል እንዲያመለክቱ እናበረታታለን፡፡ 

አስፈላጊ ስብሰባዎች/ተሳትፎዎች

  • የቦርድ አባላት መደበኛ ሰብሰባዎችን የሚሳተፉ እና በሕዝባዊ ስብሰባዎች እና ዝግጅቶች ላይ ከአከባቢው ማኅበረሰብ ለመስማት የሚሳተፉ ይሆናሉ።
  • የተንቀሳቃሽነት ቦርዱ ኦገስት 2019 (ትክክለኛ ቀኑ ወደፊት ይገለጻል) ለሁለት የግማሽ ቀናት ስልጠና (የእኩልነት እና የማህበራዊ ፍትህ ስልጠና እና የአገልግሎት እቅድ ስልጠና) እና አንድ ሙሉ ቀን ወርክሾፕ ይሰበሰባል፡፡
  • ከእነዚህ ስልጠናዎች/ወርክሾፖች በመቀጠል የለውጥ ሀሳብ መስራት ለመቀጠል እና ለማጣራት የቦርድ አባላት ከ Metro ጋር በአካል ወይም በርቀት ይጣመራሉ፡፡ ማህበረሰቡ በ2020 ፎል እና ስፕሪንግ ሊደረጉ የታሰቡ ለውጦችን የማወቅ እድል እንዲያገኝ ሀሳቡን ያጋራሉ፡፡ ይህ የቦርድ አባላት በተጨማሪ ወርክሾፖች ላይ መገናኘትን እና የመጨረሻ የግንኙነት ሀሳብን ለ King County ካውንስል ማቅረብን መደገፍ ያካትታል፡፡ 
  • የማቀድ ሂደቱ እስከ ማርች 2020 ድረስ እንደሚቆይ ይጠበቃል፡፡

 

የተንቀሳቃሽነት ቦርድ አባላት በስብሰባ/ወርክሾፕ ላይ ለሚሰሩት ስራ እና በማህበረሰቡ ውስጥ ለሚያደርጉት ተሳትፎ በሰአት $50 ካሳ ይሰጣቸዋል፡፡

 

የጥባት ዳሰሳውን ለማጠናቀቅ የሚወስደው 15 ደቂቃ አካባቢ ነው፡፡

 

የፕሮጀክት ተሳትፎ ግብ

1. በፕሮጀክቱ የጥናት ዘርፍ በታሪክ ከተጎዱ ማህበረሰቦች ጋር ትክክለኛ እና ዘላቂ ግንኙነት መገንባት፡፡

2. ተደራሽነት እና ተንቀሳቃሽነት የሚጨምር በተለይ በሽግግር ኢ-እኩልነቶች ተጽእኖ ያደረባቸው ላይ ጠንካራ የሽግግር ግንኙነት ለመገንባት በታሪክ ከተጎዱ ማህበረሰቦች ጋር በጋራ በመሆን የመጨረሻ ለውጦችን መቅረጽ፡፡

3. ከእኩልነት ውጤቶች ጋር የተያያዘ የአገልግሎት ሀሳብ ግቦችን እና የ Metro ግቦችን በጥናት ዘርፉ የአገልግሎት ሀሳቡ Metro እንዴት የእኩልነት ውጤቶችን እንደሚጨምር ለማሳየት ለሰፊው ተጽዕኖ ላደረበት ማህበረሰብ መግለጽ፡፡ 

 

የእጩነት መስፈርት

- ተጽዕኖ ባደረበት ማህበረሰብ ውስጥ የሚኖር፣ የሚሰራ ወይም የሚጓዝ (north Seattle፣ U-District፣ Shoreline፣ Bothell፣ Kenmore፣ Lake Forest Park እና Woodinvilleን ጨምሮ ግን በዚህ ሳያበቃ)

- የሽግግር ተጓዥ (የባስ አገልግሎት፣ ባር፣ የውሀ ታክሲ፣ ተደራሽነት ያላቸው አገልግሎቶች፣ የማህበረሰብ የጭነት መኪና፣ የጭነት መኪና፣ የጋራ ጭነት መኪና ወዘተ) ወይም ለሽግግር ጉዞ አቅም ያለው

- ውክልና የሌለው/ተመራጭ ያልሆነ

- ለስነ-ህዝብ መበራከት አስተዋጽኦ የሚያደርግ

- በዘር እኩልነት፣ የመጓጓዣ ችግር እና በእድል ተደራሽነት መካከል ማገናኛት የሚችል

 

የምርጫ ጊዜ፡

1. የተንቀሳቃሽነት ቦርድ ምርጫ፡ ጁን 27 - ጁላይ 22/2019

ማመልከቻ ግልጽ ይደረጋል እና ፕሮጀክት የነገራል፡፡ የ Metro ሰራተኛ በታሪክ ከተጎዱ ቡድኖች እና ተጽእኖ ከተደረገባቸው ማህበረሰቦች መካከል በግንባር ቃለ-መጠይቅ በማድረግ በንቃት ይመርጣል፡፡

2. የማመልከቻ ግምገማ እና ምርጫ፡ ጁላይ 22 – 24/ 2019

የ Metro ፕሮጀክት ቡድን ማመልከቻ (ኦንላይን እና በግንባር የገቡ ማመልከቻዎችን) ይገመግማል እንዲሁም የእጩ መስፈርት ያሟላ የቦርድ አባላትን ይለያል፡፡ የ Metro ሰራተኛ ይህን ጊዜ ከአመልካቾች ጋር ንግግርን ለማስከተል ይጠቀማል፡፡

3. የማመልከቻ ማስታወቂያ፡ ጁላይ 24 – 26/2019

ትክክለኛ አድራሻ የሰጡ ሁሉም አመልካቾች ስለመመረጥ/አለመመረጥ ይገለጽላቸዋል፡፡

4. በኦገስት በመጀመሪያዎቹ ሁለት ሳምንታት የመጀመሪያ ስብሰባ

በቦርድ አባላት የመገኘት ሁኔታ መሰረት ትክክለኛው ቀን ይገለጻል፡፡

 

የፕሮጀክት ጊዜ፡

ሰመር 2019፡ ስለሽግግር ፍላጎቶች/ተቀዳሚዎች ለማወቅ የተንቀሳቃሽነት የቦርድ ምርጫ፣ የ Metro እና MB አባላት በማህበረሰብ ዝግጅቶች ላይ የማህበረሰብ ተሳትፎ

ፎል 2019፡ የተንቀሳቃሽነት ቦርድ ጽንሰሀሳብ መደራጀት እና የማህበረሰብ ቀጣነት ያለው ተሳተፎ

ስፕሪንግ 2020፡ የግንኙነት ሀሳብ ማጠቃለል

ሰመር 2020 - ስፕሪንግ 2021፡ የማህበረሰብ ቀጣነት ያለው ተሳተፎ፤ እንደአስፈላጊነቱ ከቦርድ አባላት ጋር በግንባር በመገኘት ስብሰባዎች/የስልክ ጥሪዎች፡፡

Question title

North Link Connections የተንቀሳቃሽነት ቦርድን ለማገልገል ይፈልጋሉ እንዲሁም ይችላሉ፤ በጁላይ እና ኖቬምበር 2019 መካከል በአማካይ አራት ስብሰባዎች ላይ መገኘት?

አዎ
0%
አይ
0%
ተጨማሪ መረጃ ይፈልጋሉ
0%
Closed to responses

Question title

* እባክዎ ስምዎን እና አድራሻዎትን ያስገቡ፡፡ ከ North Link Connections ጋር ስለተያያዘ መረጃ ብቻ ነው የሚጠየቁት፡፡