የንጹህ ውሀ እቅድ መጠይቅ
ኖርዝዌስት/Northwestን ልዩ የሚያደርገው ነገር ንጹህ ውሀ ነው። ፐጌት ሳውንድ/Puget Sound፣ ሀይቆቻችን፣ ወንዞቻችን እና ጅረቶቻችን ምግብ ይሰጡናል፣ ለመጓጓዣነት ያገለግሉናል፣ የስራ እድል በመፍጠርና ለመዝናኛነት ያገለግሉናል። በሚቀጥሉት ጥቂት አስርት አመታት ውስጥ ክልሉ ለውሀ ጥራት ጥበቃ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮች ወጪ ያደርጋል። ኪንግ ካውንቲ/King County በተገቢው ጊዜ ውስጥ ተገቢ ማሻሻያዎችን ለማድረግ ያስችለው ዘንድ የፍሳሽ ውሀ እቅዱ ላይ ማሻሻያ ማድረግ ያስፈልገዋል። ይህ ጥረት የንጹህ ውሀ እቅድ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን እቅዱ የካውንቲው ስራ ለቀጣዮቹ አስርት አመታት የሚመራበት ይሆናል።
ከ 2019 ጀምሮ ኪንግ ካውንቲ/ King County ሰዎችን ስለ ውሀ ጥራት፣ የአካባቢ ጤና እና ኢኮኖሚያዊ የትኩረት አቅጣጫ በተመለከተ እያነጋረ ነው። የንጹህ ውሀ እቅዱ የሰዎችን የትኩረት አቅጣጫ እና ፍላጎቶች የሚያንፀባርቅ መሆኑን ለማረጋገጥ እንፈልጋለን።
ሰዎች መሳተፍ የሚችሉባቸው ብዙ መንገዶች አሉ። ለምሳሌ: ይህን መጠይቅ ሞልተው ለእኛ በኢሜይል መላክ፣ ቪዲዮ ማየት፣ ኤሌክትሮኒክ መጽሄታችንን ማንበብ፣ በስብሰባ ላይ እኛን ማናገር ወይም በዝግጅትዎ ላይ እኛን መጋበዝ፣ ዌቢናር መከታተል እና የመረጃ ጽሁፎችን በኦንላይን ማንበብ ይችላሉ።
የ COVID-19 ወረርሽኝ በሁላችንም ላይ ከባድ ተጽእኖ እንደፈጠረብን እናውቃለን። ግንኙነታችንን የአሁንና የወደፊት የጤናና ደህንነት ፍላጎቶችን ያገናዘበ ለማድረግ የግንኙነት መንገዶቻችንን ቀይረናል። እባክዎ ከእርስዎ ጋር ግንኙነት ለማድረግ ተመራጩን ዘዴ ለእኛ ለመንገር ለጥቂት ጥያቄዎች መልስ ይስጡ።
ይህ መጠይቅ በሚያበቃበት ወቅት ስለ እቅድ ዝግጅት ሂደቱ እና ሰዎች የሚሰጡንን ግብአት እንዴት እንደምንጠቀምበት የተመለከተ ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት ለኤሌክትሮኒክ መጽሄታችን ይመዝገቡ።